+251 911356971

ሀናን ታሪክ የ10 ሚሊዮን ብር ተከፋይ የሚያደርጋት ስምምነት አደረገች

አርቲስት ሀናን ታሪክ በቴዲ ሾው መልቲሚዲያ አምካኝነት ነው የአስር ሚሊዮን ብር የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነቱን ያደረገችው።

አርቲስት ሀናን ታሪክ የብራንድ አምባሳደር በመሆን ለ2 አመት አስር ሚሊዮን ብር የሚያስገኝ የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት አድርጋለች። ሀናን ስምምነቱን ያደረገችው ድሪመር ፉድ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ታዋቂና ግዙፍ የቻይና ኩባንያ ጋር ነው፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ያቋቋመ ሲሆን በዚህም ‹‹ኤስ›› በሚል ብራንድ ያልተለመዱና አዳዲስ የታሸጉ የኬክ ወይንም የጣፋጭ ምግቦችን እያመረተ በመላው አገሪቱ እያከፋፈለ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ ይህንን ‹‹ኤስ›› የተሰኘ ብራንድ ምርቶቹን በስፋት ለማስተዋወቅና ስርጭቱን ለማሳደግ የአንድ አመት የኮርፖሬት ብራንድ ፕሮሞሽን እቅድ ማውጣቱን ገልጿል፡፡ በዚህ እቅዱ ውስጥም ታዋቂዋን አርቲስት ሀናን ታሪክን ማካተቱን አስረድቷል፡፡ ‹‹የኤስን ብራንድ ፕሮሞሽን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ አርቲስት ሀናን እንደምትጠቅመን አምነንበታል›› ብሏል ድርጅቱ፡፡

ይህ የ10ሚሊዮን ብር ስምምነት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል ተከናውኗል።

ይህ ክፍያ በኢትዮጵያ ብራንድ አምባሳደርነት ታሪክ ሪከርድ የሰበረ ሆኖም ተመዝግቧል።

ድርጅታችን ቴዲሾው መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነቱ አካል ነው።