+251 911356971

ለፊልም ስራ ጠቃሚ ምክሮችን እና አጋዥ ስልጠናዎችን እንዲማሩ የሚያግዙ ምርጥ 5 የዩቲዩብ ቻናሎች

ብዙዎች ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን ሳያጠፉ ስለገለልተኛ ፊልም ስራ የበለጠ መማር ለሚፈልጉ ፊልም ሰሪዎች ምርጥ የፊልም ስራ ትምህርቶችን እና ምክሮችን የሚሰጡ ምርጥ የዩቲዩብ ቻናሎች አሉ። ከእነዚህ ቻናሎች መካከል አንዳንዶቹ በጣም ጥሩ ናቸው፣ አንዳንዶቹ ከአማካይ በላይ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ ለእርስዎ ምንም ዋጋ የላቸውም። በጣም ጥሩውን ለመምረጥ ይችሉ ዘንድ ይህን ቪዲዮ ቢመለከቱ ሊጥቅሞው ይችላል። ስለዚህ ፕሮፌሽናል ፊልም ሰሪ ለመሆን ሊመለከቷቸው የሚገቡ አስደናቂ የዩቲዩብ ቻናሎች ዝርዝር እነሆ ብለናል።

1. ፕሪሚየምቢት (PremiumBeat (Shameless Plug)

ፕሪሚየምቢት በዓለም ዙሪያ ካሉት ትላልቅ የቪዲዮግራፊ ብሎጎች አንዱ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለያዩ ርእሶች፣ ምክሮች እና አጋዥ ስልጠናዎች በሰፊው የሚታወቁ ግሩም የዩቲዩብ ቻናሎች ነው። ይህም በፊልም ስራ ላይ ያለዎትን ችሎታ የበለጠ እንዲያሻሽሉ ሊይግዞዎት እና ሊያነሳሱዎት ይችላል።

2. ፊልም ብሉም (PHILIP BLOOM)

የዚህ ቻናል አዘጋጅ ፊሊፕ ብሉም ስለ ፊልም ስራ ብዙ አጋዥ ትምህርቶችን የሚለቅ እና ለብዙ ፊልም ሰሪዎች ችሎታውን የማካፈል ብቃት ያለው ታዋቂ የፊልም ባለሙያ ሰው ነው። ከፊሊፕ ብሉም የዩቲዩብ ቻናል በተጨማሪ አጋዥ የሆኑ እና ጽሑፎችን ለማግኘት ግሩም ጥቆማ ይሰጣል። ከዚህ ውጪ የዩቲዩብ ቻናሉን ለሚሹ ፊልም ሰሪዎች ጥሩ ምንጭ ለማድረግ የሚያግዙ ቪዲዮዎችን ለማግኘት፣ ለመፈተሽ፣ ለመገምገም እና ለማምጣት ሲል ብቻ በተለያዩ ሀገራት ተዘዋውሯል።

3. ኢንዲ ሙጉል (INDY MOGUL (RIP)

በዚህ የዩቲዩብ ቻናል የተጫኑት ከአንድ ሺህ በላይ ጠቃሚ ምክሮች እና መማሪያዎች በመስክዎ ላይ ፕሮፌሽናል ፊልም ሰሪ ለመሆን ሊረዱዎት ይችላሉ። ከፊልም ስራ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ካሎት ከዚህ ቻናል ጥሩ መልስ ያገኛሉ።

4. ቶም አንቶስ (TOM ANTOS)

ይህ የዩቲዩብ ቻናል ለጀማሪ ፊልም ሰሪዎች ከፊልም ስራ ጋር በተገናኘ በመረጡት ሙያ የበለጠ ፕሮፌሽናል እንዲሆኑ በተዘጋጁ ብዙ አጋዥ እና አስደናቂ ዘዴዎች እና መማሪያዎች የተሞላ ነው። ከመብራት አጠቃቀም መማሪያዎች እስከ የዚህ ቻናል የቅኝት ትንታኔዎች ድረስ የተሻለ ፊልም ሰሪ ለመሆን የምትጠቀሙባቸውን ብዙ ነገሮችን ማግኘት ይችላሉ።

5. ኒውማን ፊልምስ (NEUMANN FILMS)

ነው የቪዲዮውን ይዘት በትክክል ማየት ከቻሉ ብዙ ነገሮችን ይማራሉ። ለምሳሌ በፊልሞች ላይ ቪዥዋል ኢፌክቶችን እና ቀረጻዎችን መጠቀም እንዲሁም በተለይም ፊልም ፕሮዳክሽን የሁሉም ሰው ትኩረት እንዲስብ ማድረግ። ይህ ቻናል ለፊልም ስሪዎች ጠቃሚ ምክሮች እንድሚሰጥ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ያለጥርጥር ከነዚህ ችናሎች ጠቃሚ ነገሮችን አንደሚያገኙና ችሎታዎን ማሻሻል እንደሚችሉ እናምናለን።

ከነዚህ በተጨማሪም በቴዲሾው መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን የዩቲዩብ ቻናል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን ቢመለከቱም ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ።