ፕሮፌሰር ሕይሌ ገሪማ፡ የኢትዮጵያ ሲኒማ አባት

ፕሮፊርሰር ኃይሌ ገሪማ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት ውስብስብነት በሚዳስሱ ኃይለኛ እና አነቃቂ ፊልሞች የሚታወቁ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሰሪ ናቸው። በጎንደር ከተማ የተወለዱት ሓይሌ ገሪማ ፊልም ትምህርትን ለመከታተል እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በአስራዘጠኝ ስልሳ ሰባት ወደ አሜሪካዋ ግዛት ቺካጎ በማምራት ህይወታቸን በዚያው ያደረጉ ሲሆን የባርነት እና የአፍሪካ ዲያስፖራዎችን የህመም ትሩፋት በሚያጠናው “ሳንኮፋ” በተሰኘው ፊልም እና “ጤዛ” በተሰኘው የኢትዮጵያ ታሪክ እና ፖለቲካ ጥልቅ ግላዊ ምልከታን በሚያሳየው ፊልሞቻቸው ይታወቃሉ።

የፕሮፌሰር ፋይሌ ገሪማ ስራዎች በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በማያሻማ መልኩ በማሳየት እንዲሁም ለተገለሉ ማህበረሰቦች ድምጽ ለመሆን ባላቸው ቁርጠኛ አቋም ተለይተው ይታወቃሉ። ለገለልተኛ ፊልም ስራ ደጋፊ እና በአፍሪካ እና በዲያስፖራ ሲኒማ እንቅስቃሴ ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናይ ናቸው። በዚህ እቋማቸውና ስራዎቻቸውም ከአስራሰባት በላይ አለማቀፋዊ ሽልማትጎችን አግኝተዋል።

ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ከፊልም ስራ በተጨማሪ በሃዋርድ ዩንቨርስቲ መምህር ሲሆኑ፣ ለሲኒማ ባለቸው ፍቅር ለማህበራዊ ለውጥ መሳሪያ በመሆን ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ተማሪዎች ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና በማነሳሳት ላይ ይገኛል። በአፍሪካ እና በአለም ሲኒማ ላይ ያለቸው ተጽእኖም ከፍተኛ ነው።

የፕሮፌሰር ህይሌ ገሪማ ስራዎች (የተጠቀሱት ቀናት በሙሉ እ.ኤ.አ. ናቸው)