ቪዲዮ ፕሮዳክሽን ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ ምስላዊ ይዘቶችን የምናሳይብት ሂደት ረጅም መንገድ ተጉዟል። ከመጀመሪያዎቹ የተንቀሳቃሽ ምስል ሙከራዎች እስከ ዛሬው ዲጂታል አብዮት ድረስ፣ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ታሪክ አስደናቂ ግኝት፣ የፈጠራ እና የቴክኖሎጂ እድገቶች የታሪክ ሂደት ውጤት ነው። እነዚህን በቪዲዮ ፕሮዳክሽን አለም ላይ የተፈጠሩትን ቁልፍ ምእራፎች እና ግኝቶችን እንዳስሳለን።
የተንቀሳቃሽ ምስሎች ጅማሮ:
የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ታሪክ የሚጀምረው በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ በተንቀሳቃሽ ምስሎች ፈጠራ ነው። እንደ ቶማስ ኤዲሰን እና የሉሚየር ወንድሞች ያሉ የፈጠራው ፋና ወጊዎች በፊልም ላይ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን የመቅረጽ ጽንሰ-ሀሳብ አስተዋውቀዋል፣ ይህም ለፊልም ኢንደስትሪው መሰረት ጥሏል። እነዚህ ቀደምት ፊልሞች ድምጽ አልባ እና እና ጥቁር እና ነጭ ነበሩ። ነገር ግን ተመልካቾችን የማረኩ እና አዲስ የመዝናኛ እድል የፈጠሩ ነበሩ።
የድምፅ እና የቀለም ግኝት:
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1920 ዎቹ ውስጥ፣ የተቀናበረ ድምጽ መተዋወቁ በፊልም ኢንዱስትሪው ላይ አብዮት ፈጥሯል። የንግግር ድምጾች መካተታቸው በሲኒማዊው ኢንዱስትሪ ላይ አዲስ የእውነታ ደረጃ እና ሳቢነትን ከፍ አድርጓል። ብዙም ሳይቆይ የቴክኒኮለር መምጣት በስክሪን ላይ ደማቅ ቀለሞችን አምጥቷል፣ ለታሪክ አተገባበርም አዲስ ገጽታም ጨመሯል። እነዚህ እድገቶች የተመልካቾችን የእይታ እና የማዳመጥ ልምድ በማሳደጉ በቪዲዮ ፕሮዳክሽን ላይ ትልቅ ለውጥ ፈጥሯል።
የቴሌቪዥን ዘመን:
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1950ዎቹ የቴሌቭዥን መፈጠር የቪዲዮ ስራዎችን ወደ ሰዎች ቤት አመጣ። ከፊልም ወደ ቴሌቪዥን የሚደረገው ሽግግር አዳዲስ የፕሮዳክሽን ቴክኒኮችን እና መሳሪያዎችን ጠይቋል። የቴሌቭዥን ስቱዲዮዎችም የይዘት ማምረቻ ማዕከላት ሆኑ። እንዲሁም የቪዲዮ ቴፕ መጀመሩ ቀላል የቅንብር ዘዴ እና ስርጭት እንዲኖር አስችሏል። ይህ ዘመን የቪዲዮ ፕሮዳሽን ለሰፊው ታዳሚ ይበልጥ ተደራሽ ስለመሆኑ የመጀመሪያው ምልክት መሆን ችሏል።
የዲጂታል አብዮት፡
በ20ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ የዲጂታል ቪዲዮ ፕሮዳክሽን ብቅ አለ። ኢንዱስትሪውንም እንደገና ለወጠ። የዲጂታል ካሜራዎች እና ቅደም ተከተላዊ ያልሁኑ የማቀናበሪያ ዘዴዎች መተዋወቅ የፕሮዳክሸን ሂደቱን ፈጣን፣ ተለዋዋጭ እና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ በቪዲዮ ፕሮዳክሽን አብዮት ላይ ጉልህ ለውጥ አምጥተዋል። ይህ ለውጥ ግለሰቦች እና ትናንሽ የፕሮዳክሽን ኩባንያዎች ሙያዊ ጥራት ያለው ይዘት እንዲፈጥሩ በማድረግ በቪዲዮ ፕሮዳክሽን ላይ የፈጠራ ነጻነትን ፈጥሯል።
ኢንተርኔትና ኦንላየን ቪዲዮ:
የኢንተርኔት መጀመር፣ በቪዲዮ ፕሮዳክሽን ላይአዲስ ገጽታ ፈጠረ. እንደ ዩቲዩብ እና ማህበራዊ ሚዲያ ያሉ የመሣሪያ ዘዴዎች መዘርጋት ማንም ሰው ቪዲዮዎችን ለአለም አቀፍ ታዳሚ በቀላሉ እንዲያጋራ አስችሎታል። ይህ ለይዘት ፈጣሪዎች አዳዲስ እድሎችን በመፍጠር እና የቪዲዮ ይዘትን የምንጠቀምበትን መንገድ ብዙ ተመልካችን የሳቡ ቪዲዮዎች፣ የኦንላየን አጋዥ ስልጠናዎች እና ተከታታይ ቪዲዮዎች ብቅ እንዲሉ አድርጓል።
በአጠቃላይ፣ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ታሪክ የሰው ልጅ ብልሃት እና ያላሰለሰ ፈጠራን ማሳደግ ማሳያ ነው። ከመጀመሪያዎቹ የተንቀሳቃሽ ምስሎች ሙከራዎች እስከ ዲጂታል አብዮት እና የኦንላየን ቪዲዮ ዘመን፣ እያንዳንዱ ዘመን አዳዲስ እድሎችን እና ተግዳሮቶችን ፈጥሯል። ዛሬ፣ የቪዲዮ ፕሮዳክሽን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተደራሽ መሆን ችሏል።